image
image
image
image
image

"በአንድነት የጠነከረች ብሩህ ኢትዮጵያ " በሚል መሪህ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የጎዳና ላይ የኪነጥበብ ምሽት ፕሮግራም አካሄደ።

ጥቅምት 29, 2018
"በአንድነት የጠነከረች ብሩህ ኢትዮጵያ " የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የጎዳና ላይ የኪነጥበብ ምሽት ፕሮግራም አካሄደ በመድረኩ የከተማ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች አርቲስቶች ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ሀላፊ ዶ/ር አበራ ብሩ እንደተናገሩት ጥበብ እንድታሰራራ ጥበብ ቦታዋን እንድይትዝ እና በኪነጥበብ ባለሙያዎች ተተኪ የሚፈራበትና ኪነ ጥበባዊ ስራዎች የሚገናኝበት ነው ብለዋል። ኪነ ጥበብ በህዝብና በመንግስት መሀል የሚያገናኝ ስራ ነው ያሉት ዶ/ር አበራ አያይዘው ይህ ተግባርን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። ያሉንን ሀብቶች እውቀቶች አጉልተን የምናወጣበት ሁሉም ሊሳተፍ የሚገባበት ኪነ ጥበብ ነው በማለት ዶ/ር አበራ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዘሪሁን ሽፈርዳ የአገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነው ይህን ለማጠናከር ደግሞ አሰባሳቢ ትርክትን ወሳኝ ነው። አንድ የሚያደርገንን ገዢ አሰባሳቢ ትርክት በማጠናከር የተሰሩ ስራዎችን እያጎለበትን መሄድ ይጠበቅብናል ያሉት የተከበሩ አቶ ዘሪሁን ሽፈርዳ አያይዘው አንድነታችንን የሚያጠናክሩ የአደዋ ድል እንዲሁም በኛ ዘመን የተሰራውን ዳግማዊ አድዋ የአባይ ግድብ ምስክር ነው ብለዋል። መድረኩንም የልደታ ክ/ከተማ ባህል ኪነ ጥበብ ጽ/ቤት አስተባብራል። #ልደታ_ባህልናኪነጥበብ

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች