image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት''ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት''በሚል መሪ ቃል የ2018 የኢሬቻ በዓል ሲምፖዚየም አካሄደ።

መስከረም 22, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ዘርይሁን ሽፈርዳ በመድረኩ ተገኝተው እንደገለፁት የኦሮሞ ህዝብ ሁሉን ለፈጠረ አምላኩ ከዘመን ወደ ዘመን፣ ከአንድ ወቅት ወደ ሌላ ወቅት በሰላም ስላሸጋገረው የሚያመሰግንበት፣ መጪውን ዘመን የሰላም የደስታ እንዲሆንለት የሚማጸንበት ስርዓት ነው ያሉ ሲሆን ይህን ባህል ጠብቆ ተንከባክቦና ትውፊቱን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ብለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ እንደገለፁት ኢትዮጵያ የብዙ ሀብት ፣ቅርስ፣ታሪክና ሀይማኖታዊ ስርዓት ባለቤት ናት ከእዛም መካከል የማይዳሰሰውና በዓለም አቀፍ ዩኔስኮ ላይ የተመዘገበው የገዳ ስርአት አካል የሆነው የኢሬች በዓል ተጠቃሽ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ የቅርስ ክብካቤና ጥገና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ወ/ጨርቆስ በበኩላቸው ኢትዮጵያዊነታችንን አንድነታችን አብሮነታችንን ፍቅራችንን የምንገልጽባቸው በርካታ ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ በዓላት አሉን እነሱን መንከባከብና ከማህበራዊ መስተጋብራቸው ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንድናገኝባቸው በትኩረት ልንሰራባቸው ይገባል ብለዋል። የኢሬቻ በዓል ፍጹም ሰላማዊ በሆነና ፍቅርና እርቅ ብቻ በማሳየት እንዲከበርም የሚመለከተው ባለድርሻ አካል በቅንጅት ሊሰራ ይገባልም ብለዋል ኃላፊዎቹ። ተሳታፊዎቹም በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች