የልደታ አስተዳደር ህንጻ 1ኛ ወለል
+251912987635
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
የደንበኞች አገልግሎት
የባህል እሴቶች እደ ጥበብ ሀብቶችና ቋንቋዎች ልማት ቡድን
የቅርስ ጥናትና ጥበቃ አስተዳደር ቡድን
የኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ ማበልጸግና ማስፋፋት ቡድን
የኪነ-ጥበብ ሀብቶች ልማት መድረኮች ኩነቶች ዘግጅት ቡድን
ለመልካም አስተዳደር አስተያየት
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
የአገልግሎት እርካታ አስተያየት መስጫ
ለማንኛዉም ጥያቄዎ
የጽ/ቤቱን ሮቦት ይጠይቁ
ሚዲያ
ዜና | News
ዶክመንተሪ (ቲቪ)
Video News
መጽሄት | Magazine
የፎቶ ስብስቦች
የቪዲዮ ስብስቦች
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር | Brochure
ማስታወቂያ
የአርት ስብስቦች (Art Gallery)
ይግቡ
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
መጽሄቶች | Magazine
Online TV
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Web APP
ይግቡ
ዜና | Oduu | News
ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የተሰሩ ለአገልጋግይ እና ለተገልጋይ ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ስራ
ጥቅምት 8, 2018
ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የተሰሩ ለአገልጋግይ እና ለተገልጋይ ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ስራዎች መካከል ስታንዳርዱን የጠበቀ የካቢኔ አዳራሽ ና ሚኒ የእንግዳ መቀበያ ክፍል/ሚኒ ካፌ/ ዘመናዊ የሰራተኞች ካፌ የሰራተኞች ጂም/የስፖርት መአከል/ ደረጃውን የጠበቀ የሰራተኞች ሱፐር ማርኬት የሰራተኞች ልጆች ማቆያ እና መጫወቻ ስፍራ የሰራተኞች ላይብረሪ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና መስጫ ማእከል የውስጥ እና የውጭ ካሜራ መቆጣጠሪያ ሴንተር ስታንዳርዱን የጠበቀ የወረፋ ማስጠበቂያ የተሰሩ ስራዎች እና አገልግሎት ስታንዳርድ ማሳያ ዲስፕለዮች የ2ቱን አዳራሾች ለተሰብሳቢ እንዲመቹ የማድረግ እና ዲጅታል ዙም ሚቲንግ ግብአት የስታንዳርዱን የጠበቀ የራሱ የጥገና ክፍል ያለው 3 ፑል ስቶር የ1 መአከል አገልግሎት መስጫ እና የስልጠና መአከል
ዜና | Oduu | News
"በአንድነት የጠነከረች ብሩህ ኢትዮጵያ " በሚል መሪህ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የጎዳና ላይ የኪነጥበብ ምሽት ፕሮግራም አካሄደ።
ጥቅምት 29, 2018
"በአንድነት የጠነከረች ብሩህ ኢትዮጵያ " የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የጎዳና ላይ የኪነጥበብ ምሽት ፕሮግራም አካሄደ በመድረኩ የከተማ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች አርቲስቶች ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው የክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ሀላፊ ዶ/ር አበራ ብሩ እንደተናገሩት ጥበብ እንድታሰራራ ጥበብ ቦታዋን እንድይትዝ እና በኪነጥበብ ባለሙያዎች ተተኪ የሚፈራበትና ኪነ ጥበባዊ ስራዎች የሚገናኝበት ነው ብለዋል። ኪነ ጥበብ በህዝብና በመንግስት መሀል የሚያገናኝ ስራ ነው ያሉት ዶ/ር አበራ አያይዘው ይህ ተግባርን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። ያሉንን ሀብቶች እውቀቶች አጉልተን የምናወጣበት ሁሉም ሊሳተፍ የሚገባበት ኪነ ጥበብ ነው በማለት ዶ/ር አበራ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዘሪሁን ሽፈርዳ የአገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነው ይህን ለማጠናከር ደግሞ አሰባሳቢ ትርክትን ወሳኝ ነው። አንድ የሚያደርገንን ገዢ አሰባሳቢ ትርክት በማጠናከር የተሰሩ ስራዎችን እያጎለበትን መሄድ ይጠበቅብናል ያሉት የተከበሩ አቶ ዘሪሁን ሽፈርዳ አያይዘው አንድነታችንን የሚያጠናክሩ የአደዋ ድል እንዲሁም በኛ ዘመን የተሰራውን ዳግማዊ አድዋ የአባይ ግድብ ምስክር ነው ብለዋል። መድረኩንም የልደታ ክ/ከተማ ባህል ኪነ ጥበብ ጽ/ቤት አስተባብራል። #ልደታ_ባህልናኪነጥበብ
ዜና | Oduu | News
ኪነ-ጥበብ የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን በማስጠበቅ ለትውልድ ግንባታ የሚኖረው ሚና የጎላ ነው - አቶ ግዛው አለሙ
ጥቅምት 29, 2018
በዛሬው እለት በልደታ ክፍለ ከተማ "ሀገር በቀል የሰላምና መቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል። መድረኩም የክፍለ ከተማው ባህል እና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ከሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የኪነጥበብ ባለሙያዎች፤አማተር የኪነጥበብ ቡድኖችና ጥሪ የተደረገላቸው ተገኝተዋል። በእለቱም ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የክፍለ ከተማው ባህል እና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ኪነ-ጥበብ የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን በማስጠበቅ ለሃገር ገፅታና ለትውልድ ግንባታ የሚኖረው ሚና ጉልህ ነው ብለዋል። ሃገርና ሰላም በኪነ-ጥበብ ይገለፃሉ ያሉት ኃላፊው ኪነ-ጥበብን ለበጎ አላማ በመጠቀምና የጋራ በሚያደርጉ የወል ትርክቶችን በማስረፅ ረገድ ከኪነ-ጥበብ ሰዎች ብዙ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል። ሃገር በቀል የግጭት መፍቻ መንገዶችን በኪነ-ጥበብ በመግለፅ የመከባበርና የመቻቻል እሴቶችን ለማስቀጠል ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት መቻሉን አንስተዋል። የልደታ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶሎሳ መርጋ እንደተናገሩት ሀገር በቀል የመቻቻልና የሰላም እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለው እሴቶችን በማጎልበት እረገድ የኪነጥበብ ማህበረሰቡ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ሰላም የአንድ ሀገር የማዕዘን ድንጋይና የሁሉም ነገር መሰረት ስለሆነ እንደ አይናችን ብሌን ልንጠብቀውና ልናስጠብቀው ይገባል ያሉት አቶ ቶሎሳ ሰላምን በማስፈን ረገድ በአንድነት፣ በመቻቻል እና በትብብር መስራት አለብን ሲሉ ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን በማጎልበት ለትውልድ ግንባታ በመጠቀም ሚናቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክ/ከተማ በሁሉም ወረዳዎች የ2018 የመስቀል ደመራ በዓል ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል።
መስከረም 16, 2018
የ2018 የመስቀል ደመራ በዓል በክፍለ ከተማው በሁሉም ወረዳዎች ሐይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሰላም ሠራዊት አባላት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ እንዲሁም መላው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ላደረጋችሁት የተቀናጀ ርብርብ የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ምስጋና አቅርቧል። መልካም የመስቀል ደመራ በአል። የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር!!
ዜና | Oduu | News
የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ።
ጥቅምት ጥቅምት 1, 2018
የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ። የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የማይተካ ሚናቸውን ለተወጡ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የሰላም ሰራዊት አባላት፣ የፀጥታ ሃይሎች፣ የህዝብ አደረጃጀቶችና ፎሌዎች የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ። በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ሲሆኑ የሰላምን ዋጋ በመረዳት በቅንጅት በመስራታቸው ህዝባዊ በዓላቱ ያለምንም ኮሽታ ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ርብርብ ላደረጉ አካላት በሙሉ በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለውም በዓላቱን ለማክበር የመጡ እንግዶች በሰላም ገብተው በሰላም እንዲመለሱ የተደረገው ርብርብ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል። ሰላም በማስጠበቅ ስራው ያደረጋችሁትን ርብርብ በሌሎች መደበኛ ተግባራትም በመድገም 'በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ' በሚል የጀመርነው እቅድ በማሳካት ወደ ብልፅግና የምናደርገውን ጉዞ ማፋጠን ይገባናል በማለት ወ/ሮ ልዕልቲ ጥሪ አቅርበዋል። የሰላም ሰራዊቱ አባላት በበኩላቸው እውቅናና ምስጋናው ከፍተኛ ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ገልፀው ከዚህ በኋላም ከአስተዳደሩ እና ከፀጥታ አካሉ ጋር በመቀናጀት በትጋትና ሀገራዊ የሃላፊነት ስሜት እንደሚሰሩ በጋራ ቃል ገብተዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ በጸጥታና በተለያዩ ተግባራቶች ለተሳተፉ አመራሮች፣ የጸጥታ አካላት፣ ለደንብ ማስከበር ኦፊሰሮችና ለሰላም ሰራዊት የምስጋናና የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት''ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት''በሚል መሪ ቃል የ2018 የኢሬቻ በዓል ሲምፖዚየም አካሄደ።
መስከረም 22, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ዘርይሁን ሽፈርዳ በመድረኩ ተገኝተው እንደገለፁት የኦሮሞ ህዝብ ሁሉን ለፈጠረ አምላኩ ከዘመን ወደ ዘመን፣ ከአንድ ወቅት ወደ ሌላ ወቅት በሰላም ስላሸጋገረው የሚያመሰግንበት፣ መጪውን ዘመን የሰላም የደስታ እንዲሆንለት የሚማጸንበት ስርዓት ነው ያሉ ሲሆን ይህን ባህል ጠብቆ ተንከባክቦና ትውፊቱን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ብለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ እንደገለፁት ኢትዮጵያ የብዙ ሀብት ፣ቅርስ፣ታሪክና ሀይማኖታዊ ስርዓት ባለቤት ናት ከእዛም መካከል የማይዳሰሰውና በዓለም አቀፍ ዩኔስኮ ላይ የተመዘገበው የገዳ ስርአት አካል የሆነው የኢሬች በዓል ተጠቃሽ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ የቅርስ ክብካቤና ጥገና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ወ/ጨርቆስ በበኩላቸው ኢትዮጵያዊነታችንን አንድነታችን አብሮነታችንን ፍቅራችንን የምንገልጽባቸው በርካታ ሀይማኖታዊ እና ህዝባዊ በዓላት አሉን እነሱን መንከባከብና ከማህበራዊ መስተጋብራቸው ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንድናገኝባቸው በትኩረት ልንሰራባቸው ይገባል ብለዋል። የኢሬቻ በዓል ፍጹም ሰላማዊ በሆነና ፍቅርና እርቅ ብቻ በማሳየት እንዲከበርም የሚመለከተው ባለድርሻ አካል በቅንጅት ሊሰራ ይገባልም ብለዋል ኃላፊዎቹ። ተሳታፊዎቹም በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል።
ዜና | Oduu | News
ለቀጣይ ተልዕኮ የሚመጥን የአመራር ቁመና በመላበስ የልደታን ከፍታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ።
ጥቅምት 19, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በቀጣይ 10 ቀናት የሚተገበሩ የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ ላይ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ውይይት በማካሄድ አቅጣጫ ተቀመጠ። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የህዝብንና የመንግስትን ሀላፊነት በጊዜ የለኝም መንፈስ በመስራት ከተማችን እንዲሁም ክ/ከተማው የያዙትን የልማት እና መልካም አስተዳደር ቁልፍ ተግባራት በቁርጠኝነት በማስፈፀምና በመፈፀም የተጣለብንን ሀላፊነት መወጣይ ይገባል ብለዋል። አቶ ጢቂ አያይዘው ለቀጣይ ተልዕኮ የሚመጥን የአመራር ቁመና በመላበስ የልደታን ከፍታ ለማረጋገጥ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን በትጋት፣ በቁርጠኝነት፣ በውጤት እና በስነ-ምግባር መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህ አመራር የ2018 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ከተያዙ ስትራቴጂክ ግቦች የተቀዱ የ10 ቀናት ተግባራትን መፈፀምና ማስፈፀም የሚችል የማህበረሰቡን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቁርጠኛ የሆነ፤ የሚሰጠውን ተልዕኮ አቀናጅቶ መምራትና ሀላፊነቱ በአግባቡ መወጣት የሚችል መሆን አለበት በመድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል። በመድረኩ ዋነኛ የትኩረት መስክ የሆኑት ሰዉ ተኮር ተግባራት፣ የፀጥታ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት እና የኢንሼቲቭ ስራዎችን ሌሎች የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ዜና | Oduu | News
“ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ መልእክት የኅብር ቀንን አስመልክቶ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች ተካሄደ።
መስከረም 2, 2018
በልደታ ክ/ከተማ ባህል ና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ጳጉሜ 2 የኅብር ቀንን አስመልክቶ "ብዝኀነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ መልዕክት በተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች ተካሂዷል። ዝግጅቱን በንግግር ያስጀመሩት አቶ አሰፋ ቶላ በልደታ ክ/ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ ሲሆኑ ጥንታዊና ገናና ታሪክ ካላቸዉ፣ የበርካታ እና ማራኪ ብዝኃ ሕይወት ባለቤቷ ኢትዮጵያ ብዝኃ ማንነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ያላቸውና ተፈቃቅደዉ በጋራ ታሪክ እየሠሩ የቀጠሉ ሕዝቦች ሀገር መኾኗን አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንን የሚያስተሳስሩን የጋራ ድሎች እና ታሪኮች አሉን፤ ቀደምቶቻችን በጋራ ጠላትን መክተዉ ነፃ ሀገር አስረክበውናል፡፡ እኛም በጋራ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን አሳክተናል፤ በዚህ የወል ድላችን በመስፈንጠር ኢትዮጵያን ወደ ከፍታዋ ማድረስ ይኖርብናል በማለት አቶ አሰፋ አክለው ገልፀዋል፡፡ እንደነዚህ አይነት ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች የሀገራችንን መልካም እሴቶች ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ናቸው ያሉት አቶ አሰፋ ኪነ-ጥበብ ለወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም የወል ትርክትን በማፅናት ለሀገረ መንግስት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላላቸው መሰል ዝግጅቶች ተጠናክረው መሄድ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል። የልደታ ክ/ከተማ የባህልና ዘመናዊ የኪነ-ጥበብ ቡድን በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ዝግጅቱን አድምቀውታል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ_ጥበብ ጽ/ቤት "ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የማንሰራራት ቀንና የታላቁን የህዳሴ ግድብ መመረቅ ምክንያት በማድረግ ልዩ ልዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎችንና ሁነቶችን በማቅረብ ቀኑን አክብሯል።
መስከረም 2, 2018
የክ/ከተማው ባህልና ኪነ_ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ በማንሰራራት ቀን በድምቀት የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውስጥና የውጭ ጠላቶችን አንገት ያስደፋንበትና ብልጽግናችን ዕውን እንደሚሆን ያሳየንበት ዳግማዊ አድዋችን ነው” ብለዋል፡፡ ህዳሴ ግድብ የጋራ መለያ አርማችን ኢትዮጵያ መሻገርና ማንሰራራት እንደምትችል ለአለም ያስተማርንበት ግድብ ነው ያሉ ሲሆን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተሰርቶ መጠናቀቁ በአንድነት ተባብረን ከሰራን ትልቅ ትምህርት የምንወስድበት ነው ብለዋል። የኪነጥበብ ምሽቱ በሜክሲኮ አደባባይ የተካሄደ ሲሆን የተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ለታዳሚያን የቀረቡ ሲሆን፣ የተለያዩን የኅብረተሰብ ክፍሎች በመድረኩ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ዜና | Oduu | News
ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ትኩረት ተደርጎ በመሰራቱ ተቋማዊ ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን የልደታ ክ/ከ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት አስታወቀ
መስከረም 19, 2018
የልደታ ክ/ከ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት የ2018ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የቅንጅታዊ አሰራር ዕቅድ አፈፃፀሙን ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገምግሟል። የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ግዛው አለሙ በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች በሰነድ የተደገፈ ሪፓርት የባለድርሻ አካላትን ሚናን በጥንካሬና በክፍተት የተቀመጡ ነጥቦችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆም ቅንጅታዊ አሰራርን ከተቋማት ባሻገር በየደረጃው የስራ ክፍሎችም ጎን ለጎን ተግባራዊ በማድረግ ለስራዎች ውጤታማነት መተጋገዝ እንደሚያስፈልግ ሀላፊው ገልጸዋል። የአፈጻጸም ግምገማ ለቀጣይ ስራዎቻችን ውጤታማነት ጥሩ ግብዓት የሚሰበሰብበት መድረክ መሆኑን ከጽ/ቤቱ ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ተቋማት ገልጸዋል።
ዜና | Oduu | News
በክፍለ ከተማው ተተኪ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
ጥቅምት 2, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ለአማተር የኪነጥበብ ቡድኖች የኪነ ጥበብ ሙያ ስልጠና ሰጠ። በስልጠና ላይ የልደታ ክ/ከ የባህልና ኪነ ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ እንደገለጹት ክፍለ ከተማው ለበርካታ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች መፍለቂያ ነው በማለት ይህን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ተተኪ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በተለያዩ የኪነ- ጥበብ ዘርፎች ተተኪ ከያንያንን ለማፍራት የስልጠናዉ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ገልጸው፤ ተተኪ ከያኒያን በዚህ መሠል ስልጠና ማለፍ እንደሚገባቸው ተናግረዋል። የጽ/ቤቱ የኪነጥበብ ማበልጸግ ቡድን መሪ አቶ ሀይላይ ተ/ሚካኤል በበኩላቸው በአማተር የኪነጥበቡ ቡድኖች ተደራጅተው ለሚሰሩ ወጣቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል. በስልጠናው የኪነ ጥበብ ምንነት፣ድርሰት፤ትወና፤ ዘውግ ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ብቃት ያለው የኪነ ጥበብ ባለሙያ ለመፍጠር በሁሉም ወረዳ ያሉ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ማጠናከር ስለሚገባ ስልጠናው መዘጋጀቱንና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ አቋቋመ።
ጥቅምት 1, 2018
የባህልና ኪነጥብብ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግዛው አለሙ የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ መቋቋሙ አላማዉ የቢሮዉ ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት በአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል፣ የሚጠበቅባቸዉን በዉጤታማነት እንዲወጡ የሚያግዝ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት እና ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል። ጉባኤዉ የሚተገብራቸዉ የሚወጡ መመሪያዎችና ህጎች የህዝቡን ጥቅም የጠበቁ ስለመሆናቸዉ ማረጋገጥ፣ የሚስተዋሉ የአገልግሎት ችግሮች እንዲፈቱ ምክረ ሀሳብ ማቅረብ ፣ ብልሹ አሰራሮችን መጠቆም ፣የተቋሙን አፈጻጸም መከታተል በአጠቃላይ የህዝቡ ድምጽ በመንግስት እንዲደመጥ ድልድይ በመሆን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትንና እርካታን ማረጋገጥ መሆኑን ማኑዋሉን ባቀረቡበት ወቅት ገልተዋል። በአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤዉ የልደታ ም/ቤት፣ እደጥበብ አምራች፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከኪነጥበብ በድኖች ማህበራት የተገልጋይ መማክርት ስራዉን የሚመሩ ስራ አስፈጻሚዎችም ተመርጠዋል።
ዜና | Oduu | News
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነ ጥበብ ቢሮ ባለፉት ሶስት ወራት ያከናወናቸውን ስራዎች የክ/ከተማ ባህል እና ኪነ ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ገመገመ።
ጥቅምት 6, 2018
ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ የቁልፍና የመደበኛ ስራዎች አፈጻጸምን አስመልክተው ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮው ዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ዘመነ ጥጋቡ ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ ቁልፍና መደበኛ ስራዎች አፈጻጸምን በዝርዝር አቅርበዋል። ሪፖርቱ ከአገልግሎት አሰጣ፣ ከመልካም አስተዳደርና ከመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የተከናወኑ ስራዎችን መሰረት በማድረግ የቀረበ ሲሆን በአፈጻጸም ሂደት የነበሩ ጥንካሬዎችና ውስንነቶች እንዲሁም በቀጣይ ሁለተኛ ሩብ አመት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ታሳቢ በማድረግ በዝርዝር ቀርቧል። በሪፖርቱ ላይ ባለፉት ሶስት ወራት ከባህል ዕሴት ግንባታ ስራዎች አንጻር፣ ከጷጉሜ ቀናት ከበራ ፣ዘመን መለወጫ እንዲሁም የመስቀልና የኢሬቻ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን አስመልክቶ የተከናዎኑ ስራዎች አበረታች ውጤት የተመዘገባቸው መሆኑ ተገልጿል። በተመሳሳይ መልኩ አሰባሳቢና የወል ትርክት ግንባታን ለማስረጽ በሚያስችል መልኩ ተዘጋጅተው ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሆኑ የኪነ ጥበብ ስራዎች ውጤት የተመዘገበባቸው መሆኑ ተመላክቷል። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ከተሳታፊዎች የቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን መሰረት አድርገው የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነጥበብ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንደገለጹት ባለፉት ሶስት ወራት ቢሮው በቁልፍ ተግባራትም ሆነ በመደበኛ ስራዎች አፈጻጸም ረገድ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገቡን ገልጸው በቀጣይ ሁለተኛ ሩብ ዓመትም ከዚህ የተሻለና ያደገ ውጤት ለማስመዝገብ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይ አጽኖት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
መግቢያ
ስለ_እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
ፎቶግራፎች | Photo Gallery
ቪዲዮዎች | Videos
መግለጫዎች | Press Release
መጽሄቶች | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Online TV
Web APP
ያግኙን
lidetaculture@gmail.com
+251912987635