Welcome to Lideta Subcity Culture and Art Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ የባህልና ኪነጥበብ ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና መሠረቶች አንዱ ለማድረግ ይተጋል!

በልደታ ክፍለ ከተማ
የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት

በልደታ ክፍለ ከተማ
የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት

በልደታ ክፍለ ከተማ
የባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

ኢትዮጵያ ሀገራችን የበርካታ ብሄርና ብሄረሰቦች ፣የባህላዊ እሴቶች፣ የጥንታዊ የቋንቋና የታሪክ እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የተመዘገቡ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኗ ይታወቃል፡፡ በ2022 የባህልና ኪነጥበብ ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የክ/ከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና መሠረቶች አንዱ በማድረግ፤ የክፍለ ከተማችንን ሕዝብ ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ፣ መስህቦችን በማጥናት፣ በመጠበቅ፣ በማልማት፣ በማስተዋወቅና ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ እና የከተማችንን መልካም ገጽታ በመገንባት ዘላቂ የሆነ፣ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንዲቻል በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንገኛለን፡፡ ፡፡

ጽ/ቤታችን የተሰጡት ተግባርና ኃላፊነቶችም በባህል ተፅዕኖ ሳቢያ ማህበራዊ እድገትን የሚያጓትቱ አመለካከቶችን እምነቶችንና ልማዳዊ አሰራሮችን የመለወጥ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የባህል፣ የኪነጥበብ፣ የሥነ ጥበብና የፈጠራ ችሎታ በከተማው ውስጥ እንዲያዳብርና እንዲያሰፋ የማድረግ ተግባራትን ማከናወን በአዋጅ የተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት ነው፡፡ ... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ ግዛዉ አለሙ , የልደታ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

የጽ/ቤቱ ቡድን መሪዎች

አቶ አየለ ዘሪሁን

የባህል እሴቶች እደ ጥበብ ሀብቶችና ቋንቋዎች ልማት ቡድን መሪ

አቶ ዳግማዊ ተሾመ

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ አስተዳደር ቡድን መሪ

አቶ ሀይላይ ተስፋሚካኤል

የኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ ማበልጸግና ማስፋፋት ቡድን መሪ

አቶ አንዱዓለም ጌታሁን

የኪነ-ጥበብ ሀብቶች ልማት መድረኮች ኩነቶች ዘግጅት ቡድን መሪ ተወካይ

አቶ ብሩክ ወርቁ

የኪነ-ጥበብ ሀብቶች ልማት መድረኮች ኩነቶች ዘግጅት ቡድን መሪ

የልደታ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡

ያግኙን / Contact Us

Phone: +251912987635