የልደታ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት በአዋጅ ቁ. 90/2017 መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል
- በክ/ከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ያጠናል፤ በሕግ መሠረት ይጠብቃል፤ ያስጠብቃል፤ የሀገሪቱን ብሔር ብሔረሰቦች ታሪክና ባህል ተመዝግቦ እንዲያዝ ያደርጋል፤ የባህል ሙዝየሞችን ያደራጃል፤ ያስተዳድራል፤ ቋንቋዎችና ሥነ ፅሑፎች እንዲዳብሩ ያደርጋል፤
- በባህል ተፅዕኖ ሳቢያ ማህበራዊ ዕድገትን የሚያጓትቱ አመለካከቶችን፣ እምነቶችንና ልማዳዊ አሠራሮችን የመለወጥ ተግባሮችን ያከናውናል፤
- የባህል ዘርፍ ልማታዊ አስተዋጽኦ እንዲስፋፋ ያድርጋል፤ ባህል፣ ኪነጥበብ፣ ሥነ ጥበብ እና የፈጠራ ችሎታ በከተማው ውስጥ እንዲዳብርና እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ግብረ-ገባዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን የሚያራምዱና የሚያስፋፉ እንቅስቃሴዎችን ይከታተላል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ያደርጋል፤
- በክ/ከተማዋ አስተዳደር ሥር የሚገኙ ቤተ መጽሐፍትን፤ ቤተመዛግብትና አብያተ-መዘክርን ያስተዳድራል፣ ይመራል፤ እንዲቋቋሙና እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ በባህል ዘርፍ የህዝብን ተሳትፎ መሠረት ለማስያዝ ሌሎች የባህል ተቋማት እንዲስፋፉ ያድርጋል፤
- የባህልና ቱሪዝም መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ ያሠራጫል፤
- በክ/ከተማዋ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኪነ ጥበብና የቱሪዝም ተቋማትን፣ ማህበራትን፣ ክበባትን፣ ሞያተኞችን በሕግ መሠረት ይመዘግባል፤ ፊቃድ ይሰጣል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ በባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ድጋፍ ያደርጋል፡፡