`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

በአዲ አበባ ከተማ አስተዳዳር በ2017 ዓ.ም አስፈፃሚ አካላት እንደገና ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ ቁጥር /2017 አንቀጽ የአዲስ አበባ ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡ ለቢሮው የተሰጡት ተግባርና ኃላፊነቶችም፣ በከተማዋ የሚገኙ ቤተ መፃህፍትን፣ ቤተ መዛግብትንና አብያተ መዘክርን ፣የባህል ሙዚየሞችን፣የባህል የኪነ-ጥበብ ተቋማትን እንዲያስተዳደር፣ እንዲመራ፣ እንዲያቋቁምና እንዲያስፋፋ ፣ታሪካዊ ቅርሶች የብሔር ብሔረሰቦች ታሪክና ባህል እንዲጠና እና ተመዝግቦ እንዲያዝ እንዲያደረግ፣ በባህል ተፅዕኖ ሳቢያ ማህበራዊ እድገትን የሚያጓትቱ አመለካከቶችን እምነቶችንና ልማዳዊ አሰራሮችን የመለወጥ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የባህል፣ የኪነጥበብ፣ የሥነ ጥበብና የፈጠራ ችሎታ በከተማው ውስጥ እንዲያዳብርና እንዲያሰፋ የማድረግ ተግባራትን ማከናወን በአዋጅ የተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት ነው፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. ይህ የስምምነት ሰነድ ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ዜጎች ህግና አሰራሩን ጠብቀው ያለምንም መሸራረፍ መብታቸውን በተሟላ መልኩ እንዲያገኙ ሲሆን ይህንንም ለአመራሩ፣ ለሰራተኛውም እና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ግልጽ ለማድረግ ከዚህም ባሻገር ደግሞ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በማይወጡ አካላት ላይም ተቋሙ የገባውን የህሊና ውል መሰረት አድርጎ የተጠያቂነት አሰራርን ለማጎልበት ያለመ ነው፡፡

    የዜጐች የስምምነት ሰነድ አስፈላጊነት

    1. ተገልጋዮች ቢሮው በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሆነው እርካታቸውን የሚያሻሽል አገልግሎት ለመስጠት፤
    2. ህብረተሰቡን በማሳተፍ ፍትህዊ አገልግሎት ለመስጠት፤ ተገልጋዮች በቢሮው አገልግሎት አሠጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት፤ ጥቆማና ግብዓት የሚሰጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፤
    3. ዜጎች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ (standard) ማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ፤
    4. የዜጎችን የመረጃ ማግኘት መብት ለማረጋገጥ እና ቢሮው ለዜጎች ግልፅ፤ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለበት አገልግሎት ለመሥጠት ያለመ መሆኑን ለማረጋገጥ፤

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

      የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

    ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች

    1. የባህል እሴቶችና የፎክሎር ሀብቶች /ሀገር በቀል እውቀቶች ፣ታሪካዊ ሃብቶችና ቅርሶች ጥበቃና ልማት፤ የባህል ኢንደስትሪውን የእደ ጥበብ ፈጠራ ምርቶች ገበያ ትስስርን ማጎልበት፤
    2. አንባቢ ተመራማሪና በአመክንዩ ላይ የተመሰረተ ችግር ፈቺ ዜጋ ማፍራት
    3. የኪነ-ጥበብ ፈጠራ ኢንዱስትሪ ማጎልበት
    4. ማህበረሰብ ተጠቃሚነትና አጋርነት ማሳደግ፤
    5. ተቋማዊ አቅም ግንባታ (Institional Building)፡፡

    የስትራቴጂካዊ ውጤት

    1. የተጠበቁ፣የለሙ የባህል እሴቶችና የፎክሎር ሀብቶች /ሀገር በቀል አውቀቶች፣ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ ሃብቶች፤ እንዲሁም ለስራ እድል ፈጠራ ለውጭ ምንዛሪና ለሀገር ገጽታ ግንባታ የዋለ ተወዳዳሪ የባህል ኢንደስትሪ የእደ ጥበብ ፈጠራ ምርት፤ ፣
    2. የተፈጠረ አንባቢ ተመራማሪና በአመክንዩ ላይ የተመሰረተ፣ ችግር ፈቺ የሆነ ማህበረሰብ፤፣
    3. በኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪዉ የተፈጠረ ኢንቨስትመንት ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ ያደገ የዉጭ ምንዛሪ እና የጎለበተ የሀገር ግንባታና ብሄራዊ ተግባቦት ፡፡
    4. በተፈጠረ አጋርነት ተጠቃሚ የሆነ ማህበረሰብ
    5. የተመሰረቱ ዘመናዊ ተቋማት እና የተዘረጉ አሰራሮችና ኦፕሬሽናል ስታንዳርዶች

    የደንበኞች መብቶች

    1. የመመካከር መብት፤፣
    2. ስለ አገልግሎቶቹ ሙሉ መረጃ የማግኘት፤ የመጠቀምና የሚጠይቀውን ወጭ የማወቅ፣፣
    3. ተገቢውን አገልግሎት ሳያገኝ ሲቀር ማስተካከያ የመጠየቅ፣
    4. ሁሉም አገልግሎቱን በእኩልነትና በፍትሐዊነት የማግኘትና የመጠቀም መብት፣ አላቸው።
    5. በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ጥያቄ የመጠየቅ እና ማብራሪያ የማግኘት
    6. ተገልጋዮች አገልግሎቱን በሙሉ ወይም በከፊል ለማግኘት ሲመጡ ማሟላት ያለባቸውን ሁኔታዎች በቅድሚያ የማወቅ መብት አላቻው፡፡
    7. በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አስተያየት /ቅሬታ የማቅረብ እና ላቀረቡት ጥያቄ ፍታሃዊ እንዲሁም ወቅታዊና በቂ መልስ የማግኘት፡፡
    8. ልዩ ትኩረት ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ መልኩ የመስተናገድና አገልግሎት የማግኘት፡፡
    9. በቢሮው ዕቅድ እና ግብረ-መልስ ላይ መሳተፍና አስተዋጽዖ የማድረግ፡፡

    የደንበኞች ግዴታዎች

    1. ሕጎችን እና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል፤ ፣
    2. ትክክለኛ መረጃዎችንና ማስረጃዎች የማቅረብ ፣
    3. የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታን መከተልና ማሟላት፤
    4. አገልግሎት ሰጪ ተቋሙ ተገልጋዩን በጋራ በሚከናወኑ ተግባራት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በጠየቀው ጊዜ ድርሻውን የመወጣት ግዴታ አለበት፡፡
    5. የአገልግሎት ክፍያ የመክፍል፤

    የተቋሙ ግዴታ

    1. አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ግብአቶች አሟልቶ መገኘት፣
    2. በተቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት በክብር የማስተናገድ፤
    3. ለተገልጋዮች ፍትሃዊ፤ አድሎ የሌለበት አገልግሎት የመስጠትና በእኩልነት የማገልገል፣
    4. ቅሬታና አስተያየት ለመቀበልና ለመፍታት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት የመዘርጋት፤
    5. ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፍትሀዊና ፈጣን ምላሽ የመስጠት፤
    6. ለተገልዮች የተቋሙን ዕቅድና የአፈፃፀም ሪፖርት ግልፅ ማድረግ አለበት፤
    7. በዜጎች የስምምነት ሰነድ መሰረት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላትና ተቋማዊ አቅም የመገንባት ግዴታ አለበት፡፡