image
image
image
image
image

ኪነ-ጥበብ የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን በማስጠበቅ ለትውልድ ግንባታ የሚኖረው ሚና የጎላ ነው - አቶ ግዛው አለሙ

ጥቅምት 29, 2018
በዛሬው እለት በልደታ ክፍለ ከተማ "ሀገር በቀል የሰላምና መቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል። መድረኩም የክፍለ ከተማው ባህል እና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ከሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የኪነጥበብ ባለሙያዎች፤አማተር የኪነጥበብ ቡድኖችና ጥሪ የተደረገላቸው ተገኝተዋል። በእለቱም ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የክፍለ ከተማው ባህል እና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው አለሙ በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ኪነ-ጥበብ የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን በማስጠበቅ ለሃገር ገፅታና ለትውልድ ግንባታ የሚኖረው ሚና ጉልህ ነው ብለዋል። ሃገርና ሰላም በኪነ-ጥበብ ይገለፃሉ ያሉት ኃላፊው ኪነ-ጥበብን ለበጎ አላማ በመጠቀምና የጋራ በሚያደርጉ የወል ትርክቶችን በማስረፅ ረገድ ከኪነ-ጥበብ ሰዎች ብዙ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል። ሃገር በቀል የግጭት መፍቻ መንገዶችን በኪነ-ጥበብ በመግለፅ የመከባበርና የመቻቻል እሴቶችን ለማስቀጠል ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት መቻሉን አንስተዋል። የልደታ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶሎሳ መርጋ እንደተናገሩት ሀገር በቀል የመቻቻልና የሰላም እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለው እሴቶችን በማጎልበት እረገድ የኪነጥበብ ማህበረሰቡ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ሰላም የአንድ ሀገር የማዕዘን ድንጋይና የሁሉም ነገር መሰረት ስለሆነ እንደ አይናችን ብሌን ልንጠብቀውና ልናስጠብቀው ይገባል ያሉት አቶ ቶሎሳ ሰላምን በማስፈን ረገድ በአንድነት፣ በመቻቻል እና በትብብር መስራት አለብን ሲሉ ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን በማጎልበት ለትውልድ ግንባታ በመጠቀም ሚናቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች