image
image
image
image
image

የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ።

ጥቅምት ጥቅምት 1, 2018
የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ። የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የማይተካ ሚናቸውን ለተወጡ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የሰላም ሰራዊት አባላት፣ የፀጥታ ሃይሎች፣ የህዝብ አደረጃጀቶችና ፎሌዎች የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ። በምስጋና ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ሲሆኑ የሰላምን ዋጋ በመረዳት በቅንጅት በመስራታቸው ህዝባዊ በዓላቱ ያለምንም ኮሽታ ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ርብርብ ላደረጉ አካላት በሙሉ በአስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል። ወ/ሮ ልዕልቲ አክለውም በዓላቱን ለማክበር የመጡ እንግዶች በሰላም ገብተው በሰላም እንዲመለሱ የተደረገው ርብርብ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል። ሰላም በማስጠበቅ ስራው ያደረጋችሁትን ርብርብ በሌሎች መደበኛ ተግባራትም በመድገም 'በአዲስ እይታ የልደታ ከፍታ' በሚል የጀመርነው እቅድ በማሳካት ወደ ብልፅግና የምናደርገውን ጉዞ ማፋጠን ይገባናል በማለት ወ/ሮ ልዕልቲ ጥሪ አቅርበዋል። የሰላም ሰራዊቱ አባላት በበኩላቸው እውቅናና ምስጋናው ከፍተኛ ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ገልፀው ከዚህ በኋላም ከአስተዳደሩ እና ከፀጥታ አካሉ ጋር በመቀናጀት በትጋትና ሀገራዊ የሃላፊነት ስሜት እንደሚሰሩ በጋራ ቃል ገብተዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ በጸጥታና በተለያዩ ተግባራቶች ለተሳተፉ አመራሮች፣ የጸጥታ አካላት፣ ለደንብ ማስከበር ኦፊሰሮችና ለሰላም ሰራዊት የምስጋናና የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች