የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

ኢትዮጵያ ሀገራችን የበርካታ ብሄርና ብሄረሰቦች ፣የባህላዊ እሴቶች፣ የጥንታዊ የቋንቋና የታሪክ እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የተመዘገቡ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኗ ይታወቃል፡፡ በ2022 የባህልና ኪነጥበብ ዘርፍን በማላቅ ከቀዳሚ የክ/ከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና መሠረቶች አንዱ በማድረግ፤ የክፍለ ከተማችንን ሕዝብ ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ፣ መስህቦችን በማጥናት፣ በመጠበቅ፣ በማልማት፣ በማስተዋወቅና ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ እና የከተማችንን መልካም ገጽታ በመገንባት ዘላቂ የሆነ፣ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንዲቻል በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንገኛለን፡፡ ፡፡

ጽ/ቤታችን የተሰጡት ተግባርና ኃላፊነቶችም በባህል ተፅዕኖ ሳቢያ ማህበራዊ እድገትን የሚያጓትቱ አመለካከቶችን እምነቶችንና ልማዳዊ አሰራሮችን የመለወጥ ተግባራትን እንዲያከናውን፣ የባህል፣ የኪነጥበብ፣ የሥነ ጥበብና የፈጠራ ችሎታ በከተማው ውስጥ እንዲያዳብርና እንዲያሰፋ የማድረግ ተግባራትን ማከናወን በአዋጅ የተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት ነው፡፡

አቶ ግዛዉ አለሙ , የልደታ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ
image description